This website uses cookies. You can select what type of cookies to allow. Read more about cookies and what they are used for.
Accept all Only criticalስዊድን፡ያለ፡የቤተሰብ፡አባል፡ጋር፡ሄዶ፡ለመኖር፡በሚመለከት፡ በስዊድን፡ኤምባሲ፡ለማመልከት፡ሲፈልጉ፡አስፈላጊውን፡አገልግሎት፡ከኤምባሲው፡ውጪ፡ካሉ፡ህገ-ወጥ፡ሰዎች፡ከማግኘት፡ይቆጠቡ።
አንዳንድ፡ግለስቦች፡በሀሰት፡የስዊድን፡የማይግሬሽን፡ጽ/ቤትን፡ወይንም፡በአንዳንድ፡ሀገሮች፡ያሉ፡የስዊድን፡ኤምባሲን፡እንወክላለን፡እንደሚሉ፡የስዊድን፡የውጪጉዳይ፡ሚኒስቴር፡መረጃ፡ደርሶታል።እነዚህ፡ግለስቦች፡የኤምባሲ፡መግቢያ፡ቀጠሮን፡ማሳጠር፡እንችላለን፡በማለት፡ገንዘብ፡ከባለጉዳዬችይጠይቃሉ።ስለሆነም፡ማንንኛውም፡አመልካች፡መገንብ፡ያለበት፡በየትኛውም፡ሀገር፡ያለ፡የስዊድን፡ኤምባሲ፡ሆነ፡የቆንስላጽ/ቤት፡እነዚህን፡ከመሰሉ፡ግለሰቦች ወይንም፡እንሰጣለን፡ከሚሉት፡አገልግሎት፡ጋር፡ምንም፡ዓይነት፡ግንኙነት፡የለውም።ኤምባሲ፡ለመግባት፡የሚያስችል፡ማንኛውም፡ቀጠሮ(የቃለመጠይቅቀጠሮ)ወይንም፡ለቃለመጠይቅ፡ወደ፡ኤምባሲ፡ለመምጣት፡የሚያስችል፡ቀጠሮ፡ሁሉ፡የሚያዘው፡በእያንዳንዱ፡ኤምባሲ፡ሲሆን፡ቀጠሮ፡ለመስጠት፡ማንኛውም፡የስዊድን፡ኤምባሲ፡ክፍያ፡አይጠይቅም።በሌላ፡በኩል፡ስዊድን፡ያለየቤተሰብ፡አባል፡ጋር፡ለመኖር፡የሚሞላ፡ማመልከቻን፡የሚቀበለው፡የስዊድን፡ኤምባሲ፡ብቻ፡ነው። የስዊድን፡መንግሥታዊ፡መ/ቤቶችን፡እንወክላለን፡በማለት፡በሀሰት፡የሚቀርቡ፡ግለሰቦች፡ካሉ(ካጋጠምዎ)፡ወይንም፡እንዳንድ፡አገልግሎት፡ለመስጠት፡ኤምባሲው፡ከሚጠይቀው፡የገንዘብ፡ መጠን፡በተጨማሪ፡ክፍያ፡በተለያዩ፡ግለሰቦች፡ከተጠየቁ፡በሚከተለው፡የኢሜል፡አድራሻ፡ኤምባሲውን፡ያሳውቁ። (ambassaden.addis-abeba@gov.se).
Sweden has diplomatic relations with almost all States in the world. It has embassies and consulates in around half of these. Sweden's foreign representation consists of approximately 100 missions abroad and 350 honorary consulates.